ባንተ ውስጥ ያንተን እድገት የሚቃወም ጭራቅ አለ፡፡ከድህነት እንድታመልጥ አይፈልግም፡፡ከመጥፎ ጓደኞችህ ስትሸሽ ያመዋል፡፡ከሱስ ስትርቅ ይጨንቀዋል፡፡ፍላጎቱ ለጊዛዊ ደስታ ጊዜና ሐይልህን በከንቱ እንድታባክን ነው፡፡

በተለይ አዲስ ነገር ስትሞክር ይንጫጫል፡፡

"ይህን ማድረግ አደጋ አለው!! ጎመን በጤና! ዋ! ትከስራለህ !ይሳቅብሃል!!" በማለት አዛኝ መስሎ እንደ ሐውልት ያስቆምሃል፡፡በጊዜ ሂደትም ወደኃላ ጎትቶ ይጥልሃል፡፡በገዛ ራስህ ህይወት አቅም ታጣለህ፡፡እሱ ንጉስ አንተ ባርያ ትሆናለህ::

+

ባርነት አልሰለቸህም? የራስህ ህይወት ንጉስ መሆን አላመማረህም? ከጭራቁ እስር ቤት ነጻ መውጣትስ? በፈለከው ሰዓት የፈለከውን ነገር ማድረግስ? የራስህን ህይወት መኪና መሪ መጨበጥስ?  ህልምህን አሳክተህ ከስኬት ተራራ ጫፍ መሆንስ?  አያጓጓህም? መልስህ "አዎ!" ከሆነ  በመጀመርያ በውስጥህ ያንቀላፋውን ጀግና   ቀስቅሰው፡፡

+

ባንተ ውስጥ ያንቀላፋ ምንም ነገር ማድረግ የሚችል ጀግና ሰው  አለ፡፡ይህ ጀግና ፈጣሪን የሚመስል ገራሚ ሐይል ነው፡፡ይህንን ሐይል  ማድመጥ ጀምር፡፡የጭራቁን አቅምና ሐይል ከውስጥህ ነቅሎ ይጥለዋል፡፡ 

+

ጭራቁ ማንነትህ ፈሪ ነው፡፡ጀግናው ማንነት #አማኝ ነው፡፡ጭራቁ ማንነትህ ሰነፍ ነው፡፡ጀግናው ማንነትህ #ለፊ ነው፡፡ጭራቁ ማንነትህ "ሰው ምን ይለኛል?" ይላል፡፡ስህተት ይፈራል፡፡ፍጹም መስሎ ለመታየት ይሞክራል፡፡ጀግናው ማንንትት ግን "እኔ ራሴን ምን እላለው? ፈጣሪስ ምን ይለኛል?" ይላል፡፡ፍጹም መስሎ የመታየት ምኞት የለውም፡፡እሱ የህይወት ዘመን ተማሪ ነው፡፡ ጭራቁ ማንነትህ ጊዛዊ ደስታን ብቻ ይፈልጋል፡፡ጀግናው ማንነትህ ግን ረጅሙን የውስጥ ሰላም፣ ፍቅር፣ ወሳጣዊ ደስታና ስኬት ይሻል።

Comments

Popular posts from this blog

Passion

በሳምንት አንዲት ሴት ለማናውቀው አምላክ?!